top of page
Search

“ሸረሪቶችን አትግደል ተረግመዉ ነዉ እንጂ እንዲህ የሆኑት እንደኛዉ ሰዉ ነበሩ።”

Mekonnen Teshome


(በመኮንን ተሾመ ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2012 ዓ፣ም )

በልጅነቴ ሸረሪት ለመግደል ስዉተረተር የምታየኝ አያቴ “ሸረሪቶችን አትግደል ተረግመዉ ነዉ እንጂ እንዲህ የሆኑት ፣ እንደኛዉ ሰዎች ነበሩ።” የምትለኝ አሁን አሁን የገባኝ መሰለኝ ። ዛሬ ይሄን አባባል ከሀገራዊ እዉቀት (Indigenous Knowledge) ጋር እንደሚያያዝ ተረድቻለሁ። ባህላዊ ማህበረሰቦች ተገቢ ያልሆነ ነገር እንዳይፀም የራሳቸዉን ትርክት ይፈጥራሉ። አያቴም ትርክቱን ተጥቅማ ሸረሪቶችን ታደገች።

አዎ ሸረሪቶች ጠቃሚዎች ናችዉ

ዛሬ ስለሸረሪቶች ላዎጋ ወደድኩ። ከኮሮና አንስቶ ስንት የሚያሳስቡ ጉዳዮች እያሉ ስለሸረሪቶች ማዉራቴ ጅልነት ነዉ እንዳትሉኝ። የሸረሪቶች ጉዳይ ቀላል አይደለም። በጣም ጠቃሚ ፣ አስደናቂና ዉስብስብ ሲሆነ በቅርበት በየቤታችን ያለ ጉዳይ ነዉ።

ሸረሪቶች የማይገኙበት የአለም ክፍል የለም። በአለማችን ዙሪያ ከ46000 በላይ የሸረሪት ዝርያዎች ያሉ ቢሆንም እኛ ስለነዚህ በቅርበት ስላሉ ፍጡራን ብዙም ሳይንሳዊ እዉቅት እና እይታ የለንም። ሁሉም ሸረሪቶች ጎጂዎችና አላስፈላጊ ይመስሉናል። ብዙ ስዎቸም ሸረሪቶችን በደፈናዉ ይፈራሉ። አንዳንድ የፈረንጅ ቱሪስቶችማ “አፍሪካን ልጎበኝ እፈልግ ነበርነገር ግን ነብሳተችንና ሸረሪቶች እፈራለሁ።” እያሉ ሲፅፉ በየድረ-ገፁ እናያለን። ይገርማል !

ብዙ ሸረሪቶች ከጉዳታችዉ ይልቅ ጥቅማችዉ ይበልጣል። ለምሳሌ ያህል ጥቂቶቹን ለመመልከት፦

  1. ሸረሪቶች ለግብርና በተለይ ለፍራፍሬ ምርቶች መጨመር በጣም ጠቃሚ ፍጡር ናቸው። ምክንያቱም እነሱ የሚመገቡት ወይም የሚያጠፉት የግብርና ምርቶችን ሳይሆን የግብርና ምርቶችን የሚያጠቁትን ነብሳቶች ነዉ።

  2. ሸረሪቶች የዎባ ትንኞችን ጨምሮ ሌሎችንም በሽታ አምጭ ነብሳቶችን በማጥፋትም ትልቅ ጠቀሜታ አላቸዉ።

  3. ሌላዉ ሸረሪቶች ድራቸዉነ የሚሰሩበት መንገድ ለኛ ለሰዎች ጥሩ የሃር ስራ መነሻ በመሆን ያገለግላል።

  4. አብዛኞቹ ሸረሪቶች ምንም ጉዳት የሌላቸዉና ጠቃሚዎች ሲሆኑ ጥቂተ ዝረያዎች ግን ተናዳፊና አደገኛ ናቸዉ። ታዲያ የነዚህን ሸረሪቶች መርዝ በባለሞያዎች መሰበሰበ ከተቻለ ጥሩ የመድሃኒት መስሪያ ግበአትም ሊሆን ስለሚችል ጠቀሚታቸዉ ሰፊ ነዉ።

ሸረሪቶች ልዩ ባህሪያት

በርካታ ሰዉ ሸረሪቶችን ኢንሴክት ከሚባሉት ነብሳት ጋር እንደሚመደቡ ያስባል። ነገር ግን ሸረሪቶች አራክኒድ (Arachnid) ዝርያዎች ማለትም ከነ ጊንጥ እና መሰሎቹ እንጂ ከኢንሴክቶች አይመደቡም።

ምክንያቱመ ብዙ ኢንሴክቶች ስድስት እግር ፣ ሶስት ዋና የሰዉነት ክፍልና ክንፍ ያላቸዉ ሲሆን ሸረሪቶች እግሮች እና ሁለት ዋና የሰዉነት ክፍሎች አሏቸዉ ሲኖራቸዉ ባብዛኛዉ ክንፍ የላቸዉም።

ባጠቃላይ ሸረሪቶች፦

· በዚህ አለም ላይ ከዳይኖሰሮችና ከሌሆችም ቀድመዉ የነበሩ ጥንታዊ ፍጡራን ሲሆኑ ባላቸዉ ትጋትና ታታሪነት እስካሁን ባለማችን በብዛት ተሰራጭተዉ ይገኛሁ

· ሸረሪቶች ተፈጥሮአዊ ሀርን የሚሰሩቤትን መንገድ የሰዉ ልጆች ቢያጠኑትና ቢማሩበት በጣም ጠቃሚ ይሆን ነበር። ይሁን እንጂ የሰው ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ ሸረሪት የምትጠቀምበትን የተወሳሰበ አሠራር ለመቅዳት አልቻሉም።

· አንዳንዶች ሸረሪቶች ምንም አይን የሌላቸዉ ሲሆነ ሌሎች ደሞ እስከ ስምንት የሚደርስ አይኖች አሏችዉ። በጣመ ፈጣል የሆነዉን አይምሮአቸዉንል የሃር ድር ለመስራት ፣ የሚመገቡትን ነብሳት በፍጥለት ለመያዝ እና ከአደጋ ለማምለጥ በአስደናቂ ፍጥነት ይጠቀሙበታል። ግማሽ ሴንቲ ሜትር ርዝመትና ከዝንብ አንጎል ያነሰ አንጎል ያላቸው ሸረሪቶች ፣ ውስብስብ የሆኑ የእይታ መረጃዎችን ተቀብለው በዚያ መሠረት እርምጃ በመውሰድ ይደነቃሉ

· ሸረሪቶች ባጠቃላይ ትናንሽና ትላልቅ ዝርያ በመባልም ሊታዩ የሚችሉ ሲሆን ጥቂት የሸረሪት ዝርያዎቸ ተናዳፊዎች ናቸዉ። ባጠቃላይ ግን ሸረሪቶች ጉዳት የማያደርሱ ጠቃሚ እንስሳት ናቸዉ። ለምሳሌ በእንግሊዝ ሃገር ታሪክ ዉስጥ ምነም አይነት የሞት አደጋ በሸረሪቶች ንድፊያ ተከስቶ እንደማያዉቅ ተመዝግቦ ይገኛል።

በጠቀላይ ሸረሪቶች ጠቃሚ በመሆናቸዉ ሰለነሱ የሚመለከታቸዉ ምሁራን በቋሚነት ጥናት ሊያደርጉ ይገባል። ከጥቂት ወራተ በፊት በሳይንስ ጋዜጠኝነት ዙሪያ ህንድ ሀገር በሄድኩ ጊዜ ስለሸረሪት የሚመራመሩ ሁለት ህንዳዉያን አግኝቼ ለማጋገር ቺዬ ነበር። ህንዶቹ ያላቸዉን የሸረሪት ዘርያዎች አጥንተዉ ጨርሰዉ የሸረሪት ሙዚየምም ማቋቋማቸዉንም ነግረዉኛል።

በኛ ሀገር ስላለዉ ሸረሪቶች ሁኔታ እስካሁን ያየሁተ ጥናት ስለሌለ የኛዎቹም ምሁራን በስፋት ቢያስቡበት መልካምሊሆን ይችላል።

27 views0 comments

Comments


Post: Blog2_Post
bottom of page